ይህ ፕሮጀክት ጀማሪዎች የመጀመሪያ አስተዋጾ የሚያደርጉበትን መንገድ ለማቅለል እና ለመምራት ያለመ ነው። የመጀመሪያዎን አስተዋፅዖ ለማድረግ ከፈለጉ ከታች ያሉትን ደረጃዎች ይከተሉ።
በcommand line(ተርሚናል) ካልተመቸዎት፣ የGUI መሳሪያዎችን ለመጠቀም አጋዥ ስልጠናዎች እዚህ ያገኛሉ።
በማሽንዎ ላይ ጊት(git) ከሌለዎት ፤ ይጫኑት ።
በዚህ ገጽ ላይኛው ክፍል ላይ ያለውን የfork button ጠቅ በማድረግ ይህንን ማከማቻ fork ያድርጉት። ይህ በአንተ account ውስጥ የዚህን repository ቅጂ ይፈጥራል።
አሁን fork የተደረገውን ማከማቻ (repository) ቅጂ በማሽንዎ(በኮምፒውተርዎ) ይፍጥሩ። ወደ GitHub (account)መለያዎ ይሂዱ፤ fork የተደረገውን ማከማቻ ይክፈቱ፤ ኮድ የሚለውን button ጠቅ ያድርጉ እና ከዚያ ወደ clipboard ቅዳ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ::
ተርሚናል ይክፈቱ እና የሚከተለውን የgit ትዕዛዝ run
git clone "የቀዱትን url"
"አሁን የገለበጡት url" (ያለ ጥቅስ ምልክቶቹ) የማከማቻው (የዚህ ፕሮጀክት fork) url ነው። urlን ለማግኘት የቀደመውን ደረጃዎች ይመልከቱ።
ለምሳሌ:-
git clone [email protected]:ይህ-አንተ-ነህ/first-contributions.git
'ይህ-አንተ-ነህ' የእርሶ GitHub ተጠቃሚ username ነው። አሁን በ GitHub ላይ ያለውን የመጀመሪያ አስተዋፅዖ(first-contributions) ማከማቻ ይዘቶችን ወደ ኮምፒውተርዎ እየገለበጡ ነው።
በኮምፒተርዎ ላይ ወዳለው የማከማቻ ማህደር ይግቡ (እዚያው ከሌሉ ማለት ነው!)፡
cd first-contributions
አሁን የ‹git switch› ትዕዛዝን በመጠቀም ቅርንጫፍ ይፍጠሩ፡
git switch -c የእርስዎ-አዲሱ-ቅርንጫፍ-ስም
ለምሳሌ:-
git switch -c ይሁን-አለማየሁ
አሁን የ‹Contributors.md› ፋይልን በጽሑፍ አርታኢ ውስጥ ይክፈቱ እና ስምዎትን ይጨምሩበት። በፋይሉ መጀመሪያ ወይም መጨረሻ ላይ አይጨምሩት። በመካከል የትኛውም ቦታ ላይ ያስቀምጡት። አሁን, ፋይሉን save ያድርጉ።
ወደ የፕሮጀክት ማህደሩ ሄደው ይህን ትዕዛዝ (git status
) ከፈጸሙ፣ ለውጦች እንዳሉ ያያሉ።
የ‹git add› ትዕዛዙን በመጠቀም እነዚያን ለውጦች ወደ ፈጠሩት ቅርንጫፍ ያክሉ።
git add Contributors.md
አሁን የ‹git commit› ትዕዛዙን በመጠቀም እነዚህን ለውጦች ያድርጉ፡:
git commit -m "የአስተዋጽዖ አበርካቾች ዝርዝር ውስጥ የእርስዎን-ስም ያክሉ"
'የእርስዎን-ስም' የሚለውን በስምዎ ይተኩ፡፡
ለውጦችን ወደ GitHub ይግፉ
‹git push› የሚለውን ትዕዛዝ በመጠቀም ለውጦችዎን ይግፉ፡፡
git push -u origin የእርስዎ-ቅርንጫፍ-ስም
ቀደም ብለዉ በፈጠሩት የቅርንጫፍ ስም 'የእርስዎን-ቅርንጫፍ-ስም'ን ይትኩ።
በመግፋት ላይ ማንኛውም ስህተት ካጋጠሞት ፤ እዚህ ጠቅ ያድርግ:
- Authentication Error
remote: Support for password authentication was removed on August 13, 2021. Please use a personal access token instead. remote: Please see https://github.blog/2020-12-15-token-authentication-requirements-for-git-operations/ for more information. fatal: Authentication failed for 'https://github.com//first-contributions.git/'
Go to GitHub's tutorial on generating and configuring an SSH key to your account.
በ GitHub ላይ ወደ ማከማቻዎ ከሄዱ፣ ‘compare & pull request' የሚለውን ቁልፍ ያያሉ። በዚያ ቁልፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
አሁን pull request ያስገቡ።
በቅርቡ ሁሉንም ለውጦችዎን ወደ የዚህ ፕሮጀክት ዋና ቅርንጫፍ አዋህዳቸዋለሁ። ለውጦቹ ከተዋሃዱ በኋላ የማሳወቂያ ኢሜይል ይደርስዎታል።
እንኳን ደስ ያሎዎት! ልክ እንደ አስተዋጽዖ አበርካች የሚያጋጥሙትን መደበኛ fork -> clone -> አርትዕ -> የመሳብ ጥያቄ የስራ ፍሰትን አጠናቀዋል!
አስተዋጾዎን ያጣጣጥሙ እና ወደ ድር በመሄድ ለጓደኞችዎ እና ተከታዮችዎ ያካፍሉ።(https://firstcontributions.github.io/#social-share).
ማንኛውም እርዳታ ከፈለጉ ወይም ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት የእኛን 'slack' ቡድን መቀላቀል ይችላሉ::(https://join.slack.com/t/firstcontributors/shared_invite/zt-1n4y7xnk0-DnLVTaN6U9xLU79H5Hi62w).
አሁን ለሌሎች ፕሮጀክቶች በማበርከት እንጀምር። እርስዎ ሊጀምሩባቸው የሚችሉ ቀላል ጉዳዮች ያላቸውን የፕሮጀክቶች ዝርዝር አዘጋጅተናል። በድር መተግበሪያ ውስጥ ያሉትን የፕሮጀክቶች ዝርዝር ይመልከቱ(https://firstcontributions.github.io/#project-list).
GitHub Desktop | Visual Studio 2017 | GitKraken | Visual Studio Code | Atlassian Sourcetree | IntelliJ IDEA |
ይህ ፕሮጀክት የሚደገፈው በ: